crimeEthiopiaNews

በሴቶችና ህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  በሴቶችና ህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል ተባለ::በሴቶችና ህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በማስመልከት የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት ላይ በሚገኙ ተቋማት በመገኘት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት :: ፤የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ለመከላከል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ትኩረታችን የቁጥር ጉዳይ ሳይሆን አንድም ህጻን ጥቃት ሊደርስበት አይገባም የሚለው ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህጻናት ተገቢውን የጤና ፣የስነ ልቡና ድጋፍና የፍትህ አገልግሎት ሊያገኙ እንደሚገባ የገለጹት ወ/ሮ አዳነች ፤እነዚህ ጥቃት አድራሾች ወንጀለኞች መሆናቸው ታውቆ፤ በእርቅ ለመፍታት የሚደረገውን ህገወጥ አካሄድ በመተው የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲሰጥ የህክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ የሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ በበኩላቸው በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ከመድረሱ በፊት የመከላከል ስራው ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲጸየፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት  እየሰራ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፤ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህጻናት ቤተሰቦች በአቅራቢያቸው አስቸኳይ መፍትሔ የሚያገኙበትንና የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለማድረግ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለአርትስ በላከዉ መግለጫም በጋንዲና በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የሚገኘዉ ማእከል ጥቃት ለደረሰባቸዉ ሴቶች፣ ህጻናትና ቤተሰቦቻቸው ተገቢውን ድጋፍና የተፋጠነ የፍትህ አገልግሎት የሚያገኙበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የጎላ አስተዋጽዖ አለዉ ብሏል ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button