Uncategorized

የተባበሩት መንገስታት ድርጅት ባለፈው ዓመት ብቻ በዓለም 80 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል አለ

የድርጅቱ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ በዓመታዊ ሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው የመፈናቀላቸው መንስኤዎች የርስበርስ ግጭት፣ ጥቃት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ተያያዥ ችግሮች ናቸው፡፡

አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው 79.5 ሚሊዮን ከሚሆኑት ተፈናቃዮች መካከል 26 ሚሊዮን ስደተኞች፣ 4.2 ሚሊዮን ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ከ45 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ናቸው፡፡

በየዓመቱ የሥደተኞች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ያሳሰበው ድርጅቱ በተለይ በየጊዜው የሚከሰቱ ግጭቶች እንዲቆሙ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ 

የመኖሪያ ቀያቸውን በሃይል ለቀው ከተሰደዱት መካከል የሶሪያ፣ የቬንዙዌላ፣ የአፍጋኒስታን፣ የደቡብ ሱዳን እና የማይናማር ዜጎች ሁለት ሶስተኛወረን ቁጥር ይይዛሉ ብሏል ሪፖርቱ፡፡ 

ድርጅቱ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የመላው ዓለም ስጋት የሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በስደተኞቹ ላይ የሚያሳርፈው ተፅዕኖ ከባድ መሆኑ ችግሩን የባሰ ውስብስብ ያደርገዋል ብሏል፡፡ 

ችግሩን ከመሰረቱ ለመከላከል ሀገራት የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን ማስተካከል፣ ግጭቶችን የማወገድና ዜጎቻቸውን ከሚደርስባቸው ጥቃት የመጠበቅ ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ድርጅቱ አሳስቧል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button