Uncategorized

በቀን 2 ሚሊዮን ዳቦ ማምረት የሚችለዉ የሸገር ዳቦ ፋብሪካን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መረቁ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 በቀን 2 ሚሊዮን ዳቦ ማምረት የሚችለዉ የሸገር ዳቦ ፋብሪካን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መረቁ ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሸገር ዳቦ ፋብሪካ መገንባት በምግብ ራሳችንን የመቻል ጉዞ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡የሸገር ዳቦ የዳቦ ፋብሪካ ብቻ ሳይሆን በምግብ ራሳችንን የመቻል ፍላጎታችንን እንዲሁም ከድህነት ለመውጣት እና የተሻለ ሕይወት ለመኖር ያለን ፍላጎታችንን ማሳካት እንደምንችል ያሳየንበት ነው ብለዋል።በኢትዮጵያ በ10 ወር ውስጥ ፋብሪካ ገንብቶ መጨረስ እንደሚቻል ያስመሰከርበትም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ለማሳካትም በተለያዩ አካባቢዎች ሰፋፊ የስንዴ እርሻዎች መጀመራቸውን እና የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችል ልምድም መቀሰሙን የገለጹት ዶ/ር ዐቢይ፣ “ዓላማችን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስንዴን ከውጭ ማስገባት ማቆም ነው” ሲሉ ተናግረዋል።ነገር ግን ስንዴ ማምረት ብቻ ሳይሆን ያንን ስንዴ ወደ ዳቦ መቀየር የሚያስችል ፋብሪካ ማቋቋም ስለሚያስፈልግ ያንን ለማድረግም ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር ውይይት መደረጉን ጠቅሰዋል።በሸገር ዳቦ ፕሮጀክት ላይ በርካታ የግል ተቋማት እንደተሳተፉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲሮክ ኢትዮጵያ ባለቤት ሼክ አል አሙዲ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው በፍጥነት ወደ ሥራ በመግባታቸውም ምስጋናቸውን አቀርበውላቸዋል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ቀና ምላሽ መስጠቷን እና መለስተኛ የዳቦ ፋብሪካዎችን ለማስገባት በመስማማቷ አመስግነዋል።እነዚህ አሁን የተገነባው እና ወደ ፊት የሚገነቡ ፋብሪካዎች በቀን ዳቦ ለማግኘት ለሚያዳግታቸው ሕፃናት ዳቦ እንዲያገኙ የሚያስችሉ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

ጠቅላይ ሚኒስት በንግግራቸዉ የቻይናን ተሞክሮ አስታዉሰዉ ቻይና አሁን ያለችበት የእድገት ደረጃ የደረሰችዉ ህዝቦችዋ ወደ ፌት ማየት ስለቻሉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን ወደ ፌት በመጓዝ ቅንነታቸዉን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ከዚህ ባሻገር የዱባዩ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ አልናህያንም በአዲስ አበባ አነስተኛ ፋብሪካዎችን ለማቋቋም ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል።በዚሁ መድረክ ንግግር ያደረጉት የአ.አ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከአዲስ አበባ የሚነሳ መልካም ሐሳብ ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያዳርሳል ሲሉ ተናረዋል፡፡የሸገር ዳቦ ፋብሪካ መገንባቱ የከተማውን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና እንደሚቀንስ ም/ከንቲባው ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌት ተቀን አግዘውናል ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።እንደ አሁኑ ከተጋገዝን ለሚቀጥሉት ዓመታት መንግሥት የያዘቸውን ሥራዎች በፍጥነት ማሳካት እንደሚቻል ኢንጂነር ታከለ ገልጸዉ በቀጣይም የነዋሪዎችን ጥያቄ የሚመልስ ስራዎችን አቅደናል ብለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button