AfricaSports

የካፍ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች የመጨረሻ ሶስቱ ዕጩዎች ተለይተዋል

የካፍ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች የመጨረሻ ሶስቱ ዕጩዎች ተለይተዋል

የአምናው የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች መሀመድ ሳላህ፣ የክለብ አጋሩ ሳዲዪ ማኔ እና የ2015 የክብሩ ባለቤት ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ የመጨረሻ ሶስት እጩዎች በመሆን ቀርበዋል፡፡ እንደ ባለፈው ዓመት ሁሉ እነዚህ ሶስት ተጫዋቾች የ2018 የካፍ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋችነት ክብርን ለመቀዳጀት ይፎካከራሉ፡፡

ጋቦናዊው ኮከብ ኦባማያንግ ከ2014 ጀምሮ ለአምስት ጊዜ ያህል በመጨረሻ ሶስት ተጫዋቾች እጩዎች ውስጥ በተከታታይ በመካተት ከአይቮሪኮስታዊው ኮከብ ያያ ቱሬ እና ጋናዊው አማካይ ማይክል ኢሴን ጋር ለአምስት ጊዜ ያህል በመቅረብ ስሙን አስጠርቷል፡፡

አራት ጊዜ የካፍ ኮከብ ተጫዋችነት ክብርን የተጎናፀፈው ያያ ቱሬ በዕጩነት በ2011፣ 2012፣ 2013፣ 2014ና 2015 ሲቀርብ፤ ማይክል ኢሴን ደግሞ በ2005፣ 2006፣ 2007፣ 2008ና 2009 ታጭቷል፡፡

የ26 አመቱ ግብፃዊ መሀመድ ሳላህ በአፍሪካ ኮከብ ተጫዋችነት የመጨረሻ ሶስት ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ሲካተት ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በአህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እየሰበሰበ ይገኛል፡፡

ሳላህ ባለፈው ዓመት የዓመቱ ኮከብ የተባለ ሲሆን በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፍ ታሪክ የሚሰራ ይመስላል፤ ከዚህ በፊት በተከታታይ ዓመት ክብሩን ከፍ ያደረጉ ተጫዋቾች ሴኔጋላዊው አል ሃጂ ዲዩፍ (በ2001፣ 2002)፣ ካሜሮናዊው ሳሙኤል ኢቶ (2003፣ 2004) እና ያያ ቱሬ (2011፣ 2012) ናቸው፡፡

ሌላኛው የ26 ዓመት ሴኔጋላዊ ሳዲዮ ማኔ ለሶስተኛ ዓመት ሶስቱ እጩዎች ውስጥ ሲካተት፣ በ2016 ሶስተኛ እንዲሁም በ2017 ሁለተኛ በመሆን አጠናቅቋል፡፡ ማኔ ከዲዩፍ በኋላ ይሄንን ክብር ለመቀዳጀት እየተንደረደረ የሚገኝ ሌላኛው ሴኔጋላዊ ኮከብ ነው፡፡

አሸናፊው በመጭው ማክሰኞ በሴኔጋል መዲና ዳካር ላይ በሚከናወን የሽልማት ስነ ስርዓት ይፋ ይሆናል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button