Ethiopia

በኢትዮጵያ መንገዶች በሚገባዉ መልኩ ጥገና እየተካሄደላቸዉ ባለመሆኑ ሀገሪቱን ለክስረት እየዳረጋ መሆኑን የመንገድ ፈንድ ፅ/ቤት ለአርትስ ተናገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ14፣ 2012 በኢትዮጵያ መንገዶች በሚገባዉ መልኩ ጥገና እየተካሄደላቸዉ ባለመሆኑ ሀገሪቱን ለክስረት እየዳረጋ መሆኑን የመንገድ ፈንድ ፅ/ቤት ለአርትስ ተናገረ፡፡ የመንገድ ፈንድ ፅ/ቤት ከዛሬ 23 ዓመታት በፌት መንገዶች ተገንብተዉ በሚገባዉ መልኩ ጥገና እንዲደረግላቸዉና የመንገዶችን እድሜ ለማራዘም ታስቦ በ1989 ዓ.ም  የተቋቋመ ቢሆንም በተቋቋመበት ጊዜ ሂሳብ ዛሬ ድረስ ፈንድ በመደረጉ የሀገሪቱ መንገዶች በሚገባ እንዳይጠገኑ ከማድረጉም በላይ ለከፍተኛ ኪሳራ እየተዳረገች መሆኑን ነዉ የመንገድ ፈንድ ፅ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ሀላፌ አቶ አስራት አሰሌ የነገሩን ፡፡ ፅ/ቤት በአዋጁ መሰረት ከተለዮ 4 ምንጮች ገቢ እንደሚሰበስብና ከነዛ አማራጮች ዉጪ በጊዜ ሂደት በተገኘዉ ጥናት ሌሎች አማራጮች ቢኖ ሩም ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም ይላሉ አቶ አስራት ፡፡ በመሰረታዊነት በአንድ ሀገር አንድ አዋጅ ሊፀድቅ የሚችለዉ አስከ 10 ዓመት መሆኑ ቢታወቅም የመንገድ ፈንድ ፅ/ቤት የተቋቋመበት አዋጅ ግን ለ23 ዓመታት  በመዝለቁና በዛዉ የታሪፍ ዘመን ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ሀገሪቱን ኪሳራ ላይ ይጥላታል ከዚህ ባለፈ ጥ/ቤቱ በዓመት 2.8 ሚሊዩን ብር ቢሰበስብም ለፅ/ቤቱ ከመንግስት የሚመደብለት በጀት ግን በዓመት ከ10 ሚሊዮን ስለማይበልጥ ባለሙያዎችን ቀጥሮ ማሰራት ስለማይቻል መንገዶች በሚፈለገዉ ጥራት ሊታደሱ እንዳልቻሉ ነዉ አቶ አስራ የሚናገሩት በመሆኑም ጽ/ቤቱ አሁናዊ ሁኔታዉን ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት አዋጁ እንዲሻሻል ጠይቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button