EthiopiaNews

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እቃ በሚጭነበት ወቅት በእሳት መያያዙ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ15፣ 2012 የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እቃ በሚጭነበት ወቅት በእሳት መያያዙ ተሰማ::አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በቻይና ሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እቃ በሚጭነበት ወቅት ነዉ በእሳት የተያያዘዉ።ሁሉም የአውሮፕላኑ ሰራተኞ በመልካም ደህንነት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።አየር መንገዱ አደጋውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ቦይንግ 777 ኢቲ ኤአርኤች እቃ ጫኝ አውሮፕላን እቃ ሲጭን በነበረበት ወቅት በእሳት መያያዙን ገልጿል።አውሮፕላኑ ከሻንጋይ ወደ ሳኦ ፓሎ መደበኛ የካርጎ በረራ ለማድረግ ዝግጅት ላይ የነበረ መሆኑ ነው የተነገረው።በአውሮፕላኑ ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠርም ከሚመለከታቸው ሁሉም አካላት ጋር ኢትዮጵያ በትብብር መስራቷን አየር መንገዱ አስታውቋል።የእሳት አደጋው ምክንያትም በሚመለከታቸው አካላት እየተጣራ እንደሚገኝ ተነግሯል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button