Ethiopia

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዓሉን ሲያከብር ኮቪድ19 በመከላከል ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 ሙስሊሙ ማህበረሰብ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን ሲያከብር በእምነቱ የተቀመጡ የወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን ተግባራዊ በማድረግ መሆን እንዳለበት የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እንድሪስ በዓሉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡በመግለጫቸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብም ይሁን ሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ኮሮናን በመከላከል ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የምናከብረው እንደ ቀደሙት አመታት በአንድ ላይ ተሰባስበን ሳይሆን ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በመከወን መሆን ይገባዋልም ብለዋል፡፡ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአረፋ በዓል ላይ የተቸገሩትን በመርዳትና የታመሙትን በመጠየቅ ሰብአዊ ተግባር እንዲፈጽምም ጥሪ አቅርበዋል፡፡በተጨማሪም ሰብአዊነትን በተግባር በማሳየት እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በያለበት ቦታ ሁሉ የዱዓ ፀሎት በማድረግ በአሉን እንዲያከብርም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡1 ሺህ 441ኛው የአረፋ በዓል ከነገ በስቲያ አርብ እንደሚከበር ታዉቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button