EthiopiaPoliticsRegionsSocialUncategorized

መንግስት እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ሃላፊነት ወስዶ ለዜጎች ከለላ መሆን አለበት አለ

አርትስ 07/01/2011
ይህን ያለው የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው፡፡
የዜጎች በህይወት የመኖር፣ አካል ደህንነት እና በነፃነት የመንቀሳቀስ ህገ መንግስታዊ መብት ጥሰት ሲደርስባቸው መንግስት ከለላ ሊሆን እንደሚገባና እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በመፍታት ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽኑ መስሪያቤቱ በተለያዩ ጊዜያት በሚከሰቱ ግጭቶች ዙሪያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ማቅረቡን ጠቅሰው የግጭቶቹን መባባስ ተከትሎ የሚፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነው የገለፁት፡፡
በዚህም መሰረት ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ እንዲሁም ከቄያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ተገቢውን የህግ ከለላ በማድረግ ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ መንግስት የድርሻውን እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button