Ethiopia

አንድ ባለሀብት በብርጭቆ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኬሚካል እርጭት አካሄደ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 አንድ ባለሀብት በብርጭቆ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኬሚካል እርጭት አካሄደ፡፡ባለሀብቱ ኢንጂነር መኩሪያ በየነ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል  በማሰብ  የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን በኬሚካል ሲያስረጩ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በጋራ መኖሪያ መንደሩ  ከኬሚካል ርጭቱ ጎንለጎንም የችግኝ ተከላ የተካሄደ ሲሆን፤ለእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 140  ሰራተኞችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር ባለሀብቱ ድጋፍ አድረገዋል፡፡

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ቅርኝጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ልዑል ሀይሉ በባለሀብቱ ለተደረገላቸዉ ድጋፍ አመስግነዉ ህብረተሰቡ እንደ አቅሙ መደጋገፍ አለበት ብለዋል፡፡መስሪያቤታቸዉም ኮሮናን ለመከላከል  በኬሚካል ርጭት በኩል ለሚደረግለት ጥሪ ፈጣን ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ለ140 ሰራተኞች የተደረገዉ ድጋፍም መስሪያ ቤታቸን ኮሮናን ለመከላከል ለሚሰራዉ ስራ አጋዥ ነዉ ብለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button