EthiopiaFeatured

ሁለተኛው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካለ መርሀ ግብር ከታሰበለት ጊዜ ቀድሞ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 6፣ 2012በመላው ሀገሪቱ የተከናወነው የሁለተኛው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከታሰበለት ጊዜ አንድ ወር ቀድሞ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የመዝጊያ ስነ ስርዓት በባህር ዳርከተማ እየተከናወነ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም በባህር ዳር ከተማ ቤዛዊትቤተ-መንግስት እየተከናወነ ባለው የመዝጊያ ስነ ስርዓት ተገኝተዋል።በስነስርዓቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት በሁለተኛው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር 5 ቢሊዮን ችግኝ በመትከል እቅዱን ቀድሞ መሳካት ተችሏል።መላው የኢትዮጰያ ህዝብ የተሰጠውን አደራ ተቀብሎ በእኔነት ስሜት እቅዱን ቀድሞ ማጠናቀቅ በመቻሉ ምስጋና አቅርበዋል።”ጭቃ ሳይነኩና ችግርን ሳይጋፈጡ ሀገርን ማበልፀግ አይቻልም” ያሉት ዶክተር አብይ መላው ኢትዮጰያውያን ለችግኝ ተከላው ያሳዩትን ቁርጠኝነት በሌሎች የልማት ስራዎችም ሊደግም እንደሚገባም ተናግረዋል።በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መዝጊያ ስነ ስርዓቱም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልል አመራሮች ተገኝተዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button