World News

ጀርመን ለሊባኖስ የምታደርገው ድጋፍ ገሀሪቱ ከምታርገው ሪፎርም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገለፀች::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012 ጀርመን ለሊባኖስ የምታደርገው ድጋፍ ገሀሪቱ ከምታርገው ሪፎርም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገለፀች:: የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሄይኮ ማስ ድጋፉን አስመልክተው ሲናገሩ ቤይሩት ከደረሰባት አደጋ እንድታገግም ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለሚጠብቃት የፖሊሲ መሻሻያ ጭምር ነው የምንደግፋት ብለዋል፡፡ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ጀርመን በአደጋው ከባድ ጉዳት ለደረሰባት ቤይሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የ1.18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በሊባኖስ ቀይ መስቀል በኩል አበርክተዋል፡፡

ይሄም ጀርመን ለሊባኖስ ያደረገችውን ጠቅላላ የድጋፍ መጠን ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር ከፍ አድርጎታል፡፡ ማስ ከእንግዲህ በሊባኖስ የፖለቲካው ሁኔታ በነበረበት እንደማይቀጥል ገልፀው ድጋፉ ለውጥ ለማምጣት ለሚደረገው ጥረት አጋዥ ነው ብለዋል፡፡ ሊባኖስ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማድረግ ዝግጁ ከሆነች በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ሊደግፏት ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button