Social

“የሴት ልጅ ግርዛትን የማይታገስ ህብረተሰብ እንፍጠር!” በሚል አገራዊ መሪ ቃል የሚከበረዉ የንቅናቄ መድረክ በይፋ ተከፍቷል

የሴት ልጅ ግርዛትን የማይታገስ ህብረተሰብ እንፍጠር!” በሚል አገራዊ መሪ ቃል የሚከበረዉ የንቅናቄ መድረክ በይፋ ተከፍቷል፡

 

የንቅናቄዉ ዋና ዓላማ በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን የመብት ጥሰት ለማስቆም የሚረዱ ምክረ ሃሳቦች ላይ በመወያየት ድርጊቱን ለማስቆም የሚካሄደውን ጥረት ማጠናከር ነዉ ብሏል የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፡፡

 

ሃዋሳ ከተማ ላይ በተጀመረውና ለሚቀጥሉት አራት ቀናት በሚቆየው በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ያለም ፀጋይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሴት ልጅ ግርዛትን በማስቆም ሴቶችን ጤናቸውን ሊያሰናክሉ ከሚችሉ ሁለንተናዊ ችግሮች ልንጠብቃቸው፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸውንም ልናረጋግጥላቸው ያስፈልጋል ብለዋል።

 

 

በመድረኩ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር የሴት ልጅ ግርዛትን ለመቀነስና ለማጥፋት የተቀናጀና ሁሉን አቀፍ ስልታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተው አሳስበዋል።

 

መድረኩ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፤ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተመራጭ ሴቶች ኮከስ ጋር በትብብር ያዘጋጁት ሲሆን  የሴት ልጅ ግርዛት ወቅታዊ ሁኔታ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button