Ethiopia

የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በ64 ሚሊዮን ብር የተቆፈሩ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በ64 ሚሊዮን ብር የተቆፈሩ:: ጥልቅ ጉድጓዶች በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀምሩ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።   የአስተዳደሩ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይማኖት በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት የከተማውን የውሀ አቅርቦት ለማሻሻል በመካከለኛ ጊዜ እቅድ ከተያዙ አምስት ጥልቅ ጉድጓዶች የሁለቱ ቁፋሮ ተጠናቋል ።

ጥልቅ ጉድጓዶቹ የሚያመነጩትን ውሀ ወደ ከተማው ለማድረስ የ17 ኪሎ ሜትር የመስመር ዝርጋታ መከናወኑን ተናግረዋል ። ጉድጓዶቹ በሰከንድ እስከ 54 ሊትር ውሀ የማመንጨት አቅም እንዳላቸው የገለጹት ስራ አስኪያጁ ቀሪው የሞተር ፓምፕ ተከላ ስራ ተጠናቆ በመስከረም ወር 2013 ዓም መጨረሻ ላይ ስራ እንደሚጀምሩ አመላክተዋል ። ከኢትዮጵያ ውሃ ልማት ፈንድ በተገኘ 68 ሚሊዮን ብር ብድር ሌሎች ሶስት ጥልቅ ጉድጓዶችን በአዲሱ በጀት ዓመት ለመቆፈር የቦታ መረጣና ጥናት መጠናቀቁን ገልጸዋል ። የውሃ ጉድጓዶቹ ሙሉ በሙሉ ስራ ሲጀምሩ የከተማው የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን አሁን ካለበት 42 ከመቶ ወደ 58 በመቶ ከፍ እንደሚል ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡

የጎንደር ከተማ ነዋሪ አቶ አያና ሙሉአለም በሰጡት አስተያየት "የከተማው የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት ለአመታት በመዝለቁ ነዋሪው  በመልካም አስተዳደር ችግርነት ሲያነሳው ቆይቷል" ብለዋል ። ተቋሙ በአሁኑ ወቅት በቀን እስከ 15 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ በማመንጨት ለ750ሺህ ነዋሪዎች ውሀን በፈረቃ እያሰራጨ መሆኑ ታውቋል ።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button