World News

ህንድ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብራዚልን በመቅደም ሁለተኛዋ የዓለም ሀገር ሆነች፡፡

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 ህንድ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብራዚልን በመቅደም ሁለተኛዋ የዓለም ሀገር ሆነች፡፡ ህንድ በአንድ ቀን ብቻ ከ90 ሺህ በላይ አዲስ በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ ብራዚልን ቀድማና አሜሪካንን ተከትላ ሁለተኛ ሀገር ሆናለች፡፡

አሁን ላይ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሁለተኛዋ ሀገር ስትሆን፤ በሟቾች ቁጥር ደግሞ ከዓለም ሶስተኛዋ ሀገር ያደርጋታል፡፡በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ቢሆንም መንግስት ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ የእንቅስቃሴ እቀባዎችን ዳግም ክፍት ማድረግ ጀምሯል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት ከከተሞች አልፎ ወደ ገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል እየተስፋፋ መምጣቱ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል፡፡የቫይረሱ ስርጭት በተወሰነ መልኩ ከመመርመር አቅም ማደግ ጋር የተገናኘ ሲሆን አሁን ላይ የሀገሪቱ የአንድ ቀን የመመርመር አቅም ከአንድ ሚሊዮን በላይ መሆኑም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button