Africa

የፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በገዳይ ንጥረ ነገር መሆኑን የቤተሰቡ ጠበቆች ተናገሩ ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2012 የፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በገዳይ ንጥረ ነገር መሆኑን የቤተሰቡ ጠበቆች ተናገሩ ::የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በልብ ህመም ሳይሆን በአደገኛ ንጥረ ነገር ተመርዞ ስለመሆኑ መረጃ ደርሶናል ብለዋል ጠበቆቹ፡፡ የ25 ዓመቱ አብደላ ሙርሲ ከአንድ ዓመት በፊት መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት በድንገት የጡንቻ አለመታዘዝ እና መኮማተር ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ሀኪሞች ህይዎቱን ማትረፍ አልቻሉም፡፡

በወቅቱ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን አብደላ በልብ ህመም መሞቱንና በሽታው ቀደም ብሎ እንደነበረበት በማብራራት ዘግበው ነበር፡፡ አሁን ግን የሙርሲ የቤተሰብ ጠበቆች የወጣቱ አሟሟት ከተፈጥሮ ህመም ጋር የተያያዘ ሳይሆን የወንጀል ሴራ እንዳለበት ደርሰንበታል እያሉ ነው፡፡ አብደላ በድንገተኛ ህመም በሚሰቃይበት ወቅት በቅርብ ወደሚገኝ ሆስፒታል ከመውሰድ ይልቅ ከ20 ኪሎሜት በላይ መጓጓዙ የተነገረ ሲሆን ይህም በራሱ ሌላ ጥርጣሬን ይፈጥራል ተብሏል፡፡ የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ በእስር ላይ እንዳሉ ፍርድ ቤት ቀርበው ችሎት ውስጥ በድንገት ተዝለፍልፈው በመውደቅ ህይዎታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button