Africa

የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጦር ሰራዊቱ ከመንግስት አስተዳዳሪነቱ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጦር ሰራዊቱ ከመንግስት አስተዳዳሪነቱ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡
በመፈንቅለ መንግስት የመሪነቱን ስፍራ የያዙት አል ቡርሃን ጦሩ ከፖለቲካዊ ውይይቶች ራሱን እንደሚያግል ያስታወቁ ሲሆን የሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ እንደሚፈቅድ ገልፀዋል።


የጄኔራሉ መግለጫ የተሰማው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ የሚጠይቁ መጠነ ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞዎች መቀጠላቸውን ተከትሎ ነው፡፡
አል-ቡርሃን በቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር የታጠቁ ሃይሎች ለዴሞክራሲ ሽግግሩ እንቅፋት አይሆኑም ያሉ ሲሆን የሱዳን ህዝብ የሚያስተዳድረውን መሪ የሚመርጥበት ዕድል ለመስጠት ጦሩ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።


በአል-ቡርሃን የሚመራው እና ወታደራዊና ሲቪል አባላትን ያቀፈው ገዥው ሉዓላዊ ምክር ቤት ከአዲሱ መንግስት ምስረታ በኋላ ይፈርሳልም ብለዋል። ይሁን እንጂ የዴሞክራሲ ደጋፊ ቡድኖች ይህ የጦሩ ውሳኔ ተግባራዊ ለመሆን ብዙ ጊዜ ሊወስድ ስለሚችል ወታደሮቹ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ያስችላቸዋል የሚል ስጋት ውስጥ ገብተዋል፡፡


አል-ቡርሀን መንግስት ከተቋቋመ በኋላ አዲስ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ምክር ቤት እንደሚመሰረት የገለፁ ሲሆን ከመንግስት ጋር በመሆን የደህንነት እና የመከላከያ ተግባራት እንዲሁም ተያያዥነት ጉዳዮች ኃላፊነት እንደሚወስድ መናገራቸውን አልጄዚራ ዘግቧል

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button