Ethiopia

ኢትዮጵያና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል የኒዉክለር ሃይልን ለሰላማዊ ዓለማ ለመጠቀም የተደረገ የትብብር ስምምነት ማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅ እንዲፀድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 ኢትዮጵያና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል የኒዉክለር ሃይልን ለሰላማዊ ዓለማ ለመጠቀም የተደረገ የትብብር ስምምነት ማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅ እንዲፀድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ረቂቅ አዋጅን ያቀረበ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት የ1968ቱ የኒዉክለር መሳሪያዎቹን እሽቅድድምን የሚከለክለዉ ዓለም አቀፍ ስምምነትና ከዓለም አቀፉ የአዉቶሚክ ኢነርጂ ኤጄንሲ ጋር የገብትን ስምምነት ባከበረ መልኩ የኒዉክለር ኢነርጂ ለሰላማዊ ዓለማ ለመጠቀምና ያለዉ የማህበራዊና እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለዉ በማመን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደዉ 89ኛ መደበኛ ስብሰባዉ ነዉ ወደ ምክር ቤት ያስተላለፈዉ ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለማቋቋም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ በመወያየት ቀደም ሲል በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ካርፖሬሽን ስር የነበሩና በብረታ ብረት ፣ በአዉቶሞቲቭ ፣ የእርሻ መሳሪያዎች ምርት፣ የኤሌክትሮኒክስ ፣ የካንስታራክሽን ማሽነሪና ፕላንት ፣ እንዲሁም የፓሊመር ምርት ዘርፎች የተሰማሩትን ተቋማት በኢትዮ ኢነጂነሪንግ ግሩፕ ስራ በማደራጀት የሀብት አጠቃቀሙን ዉጤታማ ለማድረግ እና ወደ ፌት አትራፌነት እንዲሸጋገር ለማስቻል የማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ዉሳኔ በማቅረብ የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መርትዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button