Ethiopia

በከተማ ልማት ዕቅድ ላይ የሚመክረው ጉባኤ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ይጀምራል::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 በከተማ ልማት ዕቅድ ላይ የሚመክረው ጉባኤ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ይጀምራል::”የብልፅግና ማዕከላት ከተሞች እና ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን እንዱስትሪን ለመገንባት በጋራ እንሰራልን”!! በሚል መሪ ሀሳብ ከጥቅምት 05 -07 2013 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር የቀጣይ 10 ዓመታት መሪ ዕቅድ ትግበራ ማስጀመሪያ ጉባኤ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

የጉባኤው ዋና ዓላማ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር ከፌዴራል፣ ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር በጋራ በመሆን ለማከናወን ያስቀመጣቸውን የቀጣይ 10 ዓመት የልማት ዕቅዶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ነው፡፡ የእስካሁን አፈጻጸማቸውን በመገምገም የተገኙ ጠንካራ ጎኖች፣ በአሰራር ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ የጋራ ምክክር ይደረጋልም ተብሏል፡፡ በጉባኤው ላይ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ አመራሮች እና የዘርፉ ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ይገኛሉ:: ተብሎ ይጠበቃል ሲል የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close