Politics

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት ጋር በመጪው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ ተወያዩ

ቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት ጋር በመጪው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ ተወያዩ።

32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ከየካቲት 3-4 ቀን 2011 “ስደተኞች፣ ከስደት ተመላሾችና ተፈናቃዮች፤ በአፍሪካ በግድ መፈናቀልን ለማስቆም ዘላቂ መፍትሄ እንፈልግ” በሚል መርህ ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ ኃላፊነቷን ለመወጣት ዝግጁነቷን  በተመለከተ እና  ሁለቱ ወገኖች ጉባኤው ከተለመደው መንገድ ለየት ባለ መልኩ ሊከናወን የሚችልባቸውን መንገዶች ተነጋግረዋል።

በተጨማሪም የጉባኤው አጀንዳ የህብረቱ የለውጥ አሰራር በአፍሪካውያን ህይወት ላይ እንዴት ትርጉም ያለው ተፅእኖ እንደሚያስከትል በበቂ የሚያስተጋባ እንዲሆንም ተስማምተዋል።

አክለውም  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት በዲሞክረሲያዊ የኮንጎ ሪፑብሊክ ሁኔታ ላይም ተወያይትዋል። መረጃውን ያገኝነው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button