World News

ጆ ባይደን ክትባት እስኪጀመር 200 ሺህ አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ሲሉ አሰጠነቀቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2013 ጆ ባይደን ክትባት እስኪጀመር 200 ሺህ አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ሲሉ አሰጠነቀቁ፡፡
አዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ይህን ያሉት አዲስ ከተቋቋመው የአሜሪካ የኮሮናቫይረስ አማካሪ ቦርድ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡

ባይደን 90 በመቶ ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ ክትባት መኖሩን ከቦርዱ በተደረገላቸው ገለጻ መስማታቸውን እንደ መልካም ዜና ቢቆጥሩትም አሁንም ገና በርካታ ወራትን መጠበቅ ግድ ስለሚል ስጋቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ባይደን ቫይረሱን በክትባትና በህክምና ማዳን እስኪቻል የፊት መሸፈኛ ማስኮችን በመጠቀም፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና አስፈላጊ መመሪያዎችን በማክበር ራሳቸውን ከበሽታው እንዲከላከሉ አሜሪካዊያንን ተማጽነዋል፡፡

ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው በይደን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሳይንሳዊ መንገዶችን እንከተላለን በማለት የገቡትን ቃል አዲስ አማካሪ ቦርድ በማቋቋም ጀምረውታል፡፡ ባይደን ባቋቋሙት አማካሪ ቦርድ ውስጥ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር በወረርሽኙ ዙሪያ መግባባት ባመቻላቸው ከስራቸው የተባረሩት ዶክተር ሪክ ብራይት ይገኙበታል፡፡ ዶክተር ብራይት ከሃላፊነታቸው የተነሱት ትራምፕ የባለሞያዎችን ምክር አይሰሙም፤ ይህም ህዝቡን አደጋ ላይ ይጥለዋል በማለት ለአሜሪካ ምክር ቤት በመናገራቸው ነው ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button