Ethiopia

መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 08፣ 2013 መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ:: የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ወገኖችን ለመቀበል እና ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የተሰደዱ ንፁሀን ዜጎችን ንብረታቸውን ለመጠበቅ ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ እና ሲመለሱም ሰላማቸውን ለማስጠበቅ መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

የትግራይ ልዩ ሀይል በሶስት ቀናት ዉስጥ እጁን ለመከላከያ እንዲሰጥና ራሱንና ህዝቡን እንዲያድን የተሰጠዉ ግዜ ገደብ በመጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻ ህግ የማስከበር ስራ ይካሄዳሉ ብለዋል፡፡ በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሺያ አባላት ለወሰዱት ሀላፊነት የተሞላበት ዉሳኔ ሊመሰገኑ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button