Africa

ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ኮትዲቯርን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ኮትዲቯርን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡ በፈረንጆቹ ኦክቶበር 31 በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ 94 በመቶ በሆነ ድምፅ አሸንፈዋል መባሉን ተከትሎ ከረር ያለ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር፡፡ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር የህገ መንግስ ማሻሻያ ሲያደርጉ ጀምሮ ነበር በሀገሪቱ ተቃውሞው የተቀሰቀሰው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ኦታራ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ያሏቸውን ተቃዋሚዎች እስር ቤት አስገብተዋቸዋል ተብለው እየተተቹ ነው፡፡ በኦታራ በዓለ ሲመት ስነስርዓት ላይ የ13 ሀገራት መሪዎች የተገኙ ሲሆን የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሪዚዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚም የበዓሉ ታዳሚ ነበሩ፡፡ ሶስተኛ ድላቸውን አስመዝግበው ቀጣዩን የአመራር ዘመናቸውን የጀመሩት ኦታራ ችግሮቻችንን በንግግር በመፍታት ሀገራችንን ተባብረን እናሳድጋት ሲሉ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ መወዳራቸውን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሳቢያ በትንሹ 85 ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል፡፡ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በፕሬዚዳንት አላኒ ኦታራና በተቀናቃኛቸው ሎረን ባግቦ መካከል በተፈጠረ የምጫ ውጤት ውዝግብ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button