Ethiopia

የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ:: የትምህርት ሚኒስቴር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና፣ በጥበብና ሂሳብ ዘርፍ የሚቀርቡ የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

መመሪያው ተወዳዳሪዎች በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና አሸናፊዎች በማያሻማ መልኩ ተለይተው ተገቢውን ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች በአውደ ጥናቱ ላይ በመሳተፍ ለረቂቅ
መመሪያው ግብአት የሚሆኑ ሃሳቦችን አንስተው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በአውደ ጥናቱ የተሳተፉ ባለሙያዎችም መመሪያው በውድድር ሂደት ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችን ለመቀነስ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ከአዲሱ የትምህርት አደረጃጀትና ሥርዓት ጋር የተጣጣመ እንዲሆንም መመሪያው በትኩረት መሰራት እንዳለበት መገለጹን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button