AfricaTech

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና የፈረንሳዩ ብሄራዊ የስፔስ ጥናት ማዕከል በጋራ ሊሰሩ ነው

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና የፈረንሳዩ ብሄራዊ የስፔስ ጥናት ማአከል በህዋ ሳይንስ ዘርፍ በጋራ ሊሰሩ ነው፡፡

ተቋማቱ በጋራ ለመስራ የሚስችላቸውን ስምምነት ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡
ስምምነቱ ከሳተላይት የሚገኙ የአየር ንብረት መረጃዎችንና መተግሪያዎችን በመጠቀም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅኖዎችን በዘላቂነት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ክትትል ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡
የህዋ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እርሻን፤ የደን ሽፋን፤ ውሃ የሚገኝባቸውን አካባቢ መለየትና መከታተል የሚያስችሉ ተግባራትን መከወን የሚያስችል እና ሌሎች ተግባራትንም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡

የሰው ሃይል አቅም ግንባታና ልውውጥ፤ የህዋ ሳይንስን ለሰላማዊ ግልጋሎት መጠቀም የሚያስችል የትብብር ዘርፍ እንዲኖር ማዕቀፍ መፍጠር፤ የትብብር መስኮች ወደ ትግበራ የሚገቡበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸትም የስምምነቱ አካል  ናቸው ተበሏል ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር  ዶክተር ሰለሞን በላይ እና የፈረንሳዩ ብሄራዊ የስፔስ ጥናት ማአከል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጄን-የቭስ ሊ ጋል  ፈርመውታል፡፡

በሂልተን ሆቴል የተካሄደው የስምምነት ፊርማ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርጉት የትብብር ስምምነት አካል መሆኑ ተነግሯል
ዘገበው የኢኖቪሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button