World News

በእንግሊዝ በሙከራ ሂደት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት መልካም ውጤት እያሳየ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣ 2013 በእንግሊዝ በሙከራ ሂደት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት መልካም ውጤት እያሳየ ነው ተባለ፡፡ የክትባቱ የውጤታማነት ደረጃ ሲለካ 89 ነጥብ 3 በመቶ እንደሆነ የእንግሊዝ የጤና ባለሙያዎች ይፋ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይህን መልካም ዜና እንደሰሙ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

ኖቫቫክስ የተባለው ይህ ክትባት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመከላከል ውጤታማ ሆኖ የተገኘ ብቸኛው ግኝት ነው ተብሏል፡፡ እስካሁን እድሜያቸው ከ18 እስከ 84 ባሉ በርካታ ሰዎች ላይ ተሞክሮ አጥጋቢ ውጤት ማሳየቱ ነው የተነገረው፡፡ ክትባቱ በቅርቡ በሀገሪቱ እውቅና ሰጭ አካል ማረጋገጫ ተሰጥቶት ለህዝቡ ይከፋፈላል የሚል ተስፋ እንዳለው አምራች ኩባንያው ገልጿል፡፡

በሙከራው ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን ከነዚህ መካከል 27 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የሙከራ ደረጃው ሶስተኛ ምዕራፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን ውጤቱም ከወዲሁ ትልቅ የተስፋን ያሳየ በመሆኑ ተነግሯል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button