Africa

ሞቃዲሾ ውስጥ የደረሰ የቦንብ አደጋ የሞትና የአካል ጉዳት አድርሷል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ጥር 24፣ 2013 ሞቃዲሾ ውስጥ የደረሰ የቦንብ አደጋ የሞትና የአካል ጉዳት አድርሷል ተባለ:: አደጋው የተፈፀመው በማዕከላዊ ሞቃዲሾ በሚገኘው አፍሪክ ሆቴል ላይ ሲሆን ታጣቂዎች በአካባቢው ሁከት ከፈጠሩ በኋላ ፍንዳታው መከተሉን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ በአደጋው ሳቢያ አንድ ጡረተኛ የጦር ጄኔራልን ጨምሮ አምስት ሰዎች ህይዎታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ከሟቾቹ በተጨማሪ 10 ሰዎች በአደጋው ምክንያት የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ አደጋው የተከሰተው ሶማሊያ በቅርቡ ፕሬዚዳንታዊና የምክር ቤት ተዘዋዋሪ ምርጫ ለማካሄድ በተዘጋጀችበት ወቅት መሆኑ ለሀሪቱ መጥፎ ጊዜ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

የሶማሊያ የጸጥታ ሃይሎች በሰጡት መግለጫ ጥቃቱን ካደረሱት የአልሸባብ ታጣቂዎች መካከል ሶስቱን መግደላቸውንና አራተኛው ቀድሞ በፍንዳታው መሞቱን ተናግረዋል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞሀመድ ሁሴን ሮቤል በአደጋው ሳቢያ ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች የሀዘን መግለጫ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ለደረሰው ጥቃትና ጥቃቱ ላስከተለው ጉዳት አልሸባብ የተባለው ታጣቂ ቡድን ሙሉ ሀላፊነቱን መውሰዱን ዘገባው አመላክቷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button