World News

ዩናይትድ አርብ ኤሚሬት በእስራኤል የሚያገለግላትን አምባሳደር ሰየመች፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 ዩናይትድ አርብ ኤሚሬት በእስራኤል የሚያገለግላትን አምባሳደር ሰየመች፡፡ መሃመድ አል ካጃ በእስራኤል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር ሆነው ተሾመዋል፡፡ መሃመድ አል ካጃ በሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ ጠ/ሚኒስትር እና የዱባይ ገዥ ሼክ መሀመድ ቢን ራ
ሺድ ፊት እሁድ ዕለት በአቡ ዳቢ የአል-ዋታን ቤተመንግስት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

ሚስተር አል ካጃ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ሕገ- መንግስት እና ሌሎች ህጎች በማክበር ለብሔራዊ ጥቅሟ መከበር ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ቃል
ገብተዋል፡፡ ዩናይትድአርብ፤ኤሚሬት ከእስራኤል ጋር ያላትን ወዳጅነት እና ትብብር ለማጠናከር እንዲሰሩ ለሚስተር  አል ካጃ መመሪያ በመስጠት በተልእኳቸው ስኬታማ  እንዲሆኑ  ሼክ መሐመድ ምኞታቸውን ገልጸዋል ሲል ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button