EthiopiaPoliticsRegionsSocial

በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባንዲራንም ስለሚያጠቃልል የሌላኛውን አስተሳሰብ መግፋት አይገባም አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

አርትስ 03/01/2011
በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባንዲራንም ስለሚያጠቃልል የሌላኛውን አስተሳሰብ መግፋት አይገባም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
በመግለጫቸውም፥ በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ ብቸኛ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሆነ ከውጭ የሚገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የማግለል አካሄድን ሊከተሉ አይገባም ብለዋል።
በተናጥል በመፎከር አሸናፊ መሆን ስለማይቻል ተነጋግሮ በመግባባት መተባበር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ።
ተፎካካሪ ፖለቲከኞች በሰጥቶ መቀበልና በመተባበር በኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባንዲራንም የሚያጠቃልል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ ሰንደቅ አላማን ምክንያት በማድረግ ሀገርን ለማበጣበጥ መሞከር ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ምከንያት ለውድመት፣ ለግጭት እንዳይዳረግም አሳስበዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button