Ethiopia

አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ::

አዲስ አበባ፣  ሚያዚያ ፡ 04፣ 2013 አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ:: አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ሁሉ ምቹ ከተማ ለማድረግ የተለያዩ የልማት ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። የከተማ አስተዳደሩ የአርሶ አደር መንደሮችን ተዳራሽ ማድረግ የሚያስችሉ የመንገድ ስራፕሮጀክቶችን አስጀምሯል።

የከተማ መስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እናዳሉት ከተማዋ ለሁሉም ነዋሪቿ ምቹ እንድትሆን እየተሰራ ይገኛል።አዲስ አበባ ሁሉንም ማእከል ያደረገ ልማት ካልተከናወነባት መሀሏ ብቻ ቢለማ ስሟንየሚመጥን ና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አይሆንም ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ።

በመሆኑንም ከተማዋ ለአርሶ አደሩም፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚተዳደሩትም ሆነ ለባለሀብቱ የተመቸች መሆን አለባት ነው ያሉት።ይህንን እውን ለማድረግም የከተማ አስተዳደሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል። የከተማ አስተዳደሩ መንገዶች ባለስልጣን ኢንጀነር ሞገስ ጥበቡ፤ ከተማዋ በመንገድ ዘርፍ ያሏትን ችግሮች የመፍታት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።በተለይም የከተማዋ ደርቻ አካባቢ ያሉ የአርሶ አደር መንደሮች ለከተማዋ የቅርብ እሩቅ ሆነው መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button