Ethiopia

የአብን የሰላማዊ ትግል ጥሪ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 አብን በአማራ ሕዝብ ላይ ለተፈፀሙት ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ብሔራዊ እውቅና እንዲሰጥ ፀየቀ ፡፡ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አማራ በገዛ ሀገሩ እንደጠላት መታየቱ ማክተም እንዳለበትና ለደረሰበት በደል ይቅርታ እንዲጠየቅም አሳስቧል፡፡ በክልሉ ህዝብ ላይ ለዓመታት የቀጠለው የጅምላና የተናጥል ግድያ እንዲሁም ጅምላ ማፈናቀልን ለማስቆም የፌደራሉም ሆነ የክልሉ መንግስት ምንም አይነት ፍላጎት የሌላቸው መሆኑን ታዝቤያለሁ ያለው ፓርቲው ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እዲጣራ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸመው ጥቃት ከሞት ተርፈው፣ ንብረታቸው ወድሞና ተዘርፎ ለስደትና ለጅምላ መፈናቀል ተዳርገው በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖች የተሟላ የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ እና የካሳ ክፍያ ሊሰጣቸው እንደሚገባም ገልጿል፡፡ ደርጊቱ እንዲቆም በተለያዩ አካባቢዎች በሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች በማናቸውም ሁኔታ የግልም ይሁን የመንግስት ንብረት ላይ ምንም አይነት ጥቃት እንዳይፈፀም ህዝቡ ራሱ ነቅቶ መጠበቅ አለበት ሲልም
አሳስቧል፡፡

ሰልፈኞቹ በየትኛውም እንቅስቃሴ ከጸጥታ አካላትና ተያያዥ የመንግስት ተቋማት የጋራ መግባባትና ቅንጅት ፈጥሮ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ያለው አብን ሰላማዊ እንቅስቃሴውን አቅጣጫውን ለማሳት የሚሞክሩ ሃይሎችን በጋራ መከላከል እንደሚስያፈልግም ገልጿል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button