Ethiopia

የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ሙዚየም ማቋቋም በትውልዱ ላይ የሃገር ፍቅር ስሜት ለማስረጽ አቅም አለው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ሙዚየም ማቋቋም በትውልዱ ላይ የሃገር ፍቅር ስሜት ለማስረጽ አቅም አለው ተባለ:: የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ወታደራዊ ሙዚየም በኢትዮጵያ በሚኖረው ፋይዳ፣ ተግዳሮትና መልካም አጋጣሚዎች ዙሪያ የምክክር አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።
በአውደ ጥናቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት፣ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ተወካዮችና የቀድሞ ሰራዊት አባላት አባላት ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት ባለፈው ትውልድና በአሁኑ ትውልድ በወታደሩ እየተከፈለ ያለውን መስዋዕትነት ለመዘከር ወታደራዊ ወመዘክር ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል። በተለይም ወታደራዊ ሰነዶችን በአግባቡ መሰነድ እና ሙዚየም ማደራጀት በህብረተሰቡ እና በሰራዊቱ መካከል መቀራረብ እንዲፈጠር አስተዋጽኦው የጎላ ይሆናል ተብሏል። በተጨማሪም ለሃገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ አንድ አማራጭ ሆኖ በመምጣት ኢኮኖሚ ፋይዳ ይኖረዋልም ነው የተባለው። በጥናትና ምርምር ረገድም ግብዓት የመሆን አቅም እንደሚሆን በአውደ ጥናቱ ላይ በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ተመላክቷል። ለወታደራዊ ቅርስ ማሰባሰቡ እና ወታደራዊ ሙዚየምን በማደራጀቱ ተግባር ሁሉም ሊረባረብ ይገባልም ነው የተባለው።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button