Ethiopia

መንግሰት ስለ ኬሚካል ጦር መሳሪያዉ የሰጠዉ ምላሽ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅሟል የሚለውን ዘገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባበለ፡፡የውጭ ጉዳይ  ሚኒስቴር ሁኔታውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በቴሌግራፍ መፅሄት ላይ ታትሞ የወጣውን በትግራይ ክልል ከጦር ወንጀል የማይተናነስ ድርጊት መፈፀሙን የሚያመላክት ሪፖርት አጥብቆ እንደሚቃወም ገልጿል፡፡

በመፅሄቱ የአፍሪካ ዘጋቢ  የሆነው ዊል ብራውን መቀመጫውን ናይሮቢ ላደረገው የቴሌግራፍ መፅሄት ባጠናቀረው ፅሁፍ በትግራይ ክልል በርካታ ንፁሃን ዜጎች በኬሚካል ጦር መሳሪያ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት የተከለከሉ ጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማ አታውቅም ወደፊትም አታደርገውም ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃውን መሰረተ ቢስ  ሲል አጣጥሎታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አክሎም ኢትዮጵያ የፈረመቸውን ዓለም ቀፍ ውል ለመፈጸም ብቻ ሳይሆን ራሷ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ሰለባ ስለነበረች በየትኛውም  ስፍራ በማንኛውም ሰው ላይ ዳግም መሳሪያው ጥቅም ላይ እዳይውል አጥብቃ ታወግዛለች ብሏል፡፡ይህን መሰል ሀላፊነት የጎደለው ዘገባ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ከማሳሳትና ግጭትን ከማባባስ ባሻገር በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና ለማሳደር የተጀመረው ዘመቻ አንዱ አካል አድርጎ እንደሚያየውም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button