Politics

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ራሳቸዉን ከምርጫ አገለሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013  ለመጪው ሀገራዊ ምርጫ በግል ለመወዳደደር ተመዝግበው የነበሩት ኡስታዝ አህመድ ጀበል በምርጫው እንደማይሳተፉ ተናገሩ፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫው ለመሳተፍ እንቅስቃሴ እያደረጉ የቆዩ ቢሆንም በግል ምክንያት እራሳቸውን ማግለላቸውን በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ኡስታዝ አህመዲን ጀበል 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጅማ ከተማ ተወካይ ለመሆን እጩ ሆነው ቀርበው ነበር። በራሴ የግል ምክንያት ልቀጥል አልቻልኩም ያሉት ኡስታዝ ለጅማ ከተማ ነዋሪዎችም ይቅርታን
ጠይቀዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button