Uncategorized

የቻይና መንግስት ህገ ወጥ አዘዋዋሪ ነው- አንቶኒ ብሊንከን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013 አሜሪካ ቻይናና ሩሲያን ጨምሮ ከ10 በላይ ሀገሮችን በህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርና በግዳጅ የጉልበት ብዝበዛ ከሰሰች፡፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰጡት መግለጫ ከሩሲያና ቻይና በተጨማሪ
ማይናማር እና ቱርክ በዚሁ ተግባር ይሳተፋሉ የሚል ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ ብሊንከን በተለይ ሺንጂያንግ ግዛት አካሂዶታል ያሉትን የጅምላ እስር እና ተያያዥ ተግባራትን በመጥቀሽ የቻይና መንግስት ህገ ወጥ አዘዋዋሪ ነው ሲሉ በቀጥታ ተናግረዋል፡፡

ብሊንከን ይህን ያሉት ዓለም አቀፍ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ ሪፖርት ባደረጉበት ወቅት ቱርክ ህፃናትን ለውትድርና አገልግሎት በመመልመል ህገ ወጥ ስራ ላይ ተሰማርታለች ብለዋል፡፡ የኩባ መንግስትም ላለፉት አስር ዓመታት ህክምናን ተገን በማድረግ ከህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ጉልበት ብዝበዛ ዳጎስ ያለ ትርፍ አግኝቷል ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒትሩ፡፡

በትክክል ቁጥሩን ማስቀመጥ ባይቻልም በዓለማችን 25 ሚሊዮን የሚጠጎ ሰዎች የህገ ወጥ ዝውውር ሰለባዎች መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ዋሽንግተን አጥንቸ ደረስኩበት ያለችውን መረጃ ይፋ ስታደርግ በዓለማችን 17 የሚሆኑ ሀገራት ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የሚያደርጉት ጥረት እዚህ ግባ የማይባል ነው ብላለች፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button