Africa

ግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት አባላት ላይ የዕድሜ ልክ እስራ  ውሳኔ አስተላለፈች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 ግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት አባላት ላይ የዕድሜ ልክ እስራ  ውሳኔ አስተላለፈች፡፡
የሀገሪቱ ከፍተኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የፖሊስ አባላትን በመግደልና እስር ቤት ሰብረው እስረኞችን በማስመለጥ ወንጀል በተከሰሱ የህብረቱን መሪ ሞሐመድ ባዴን ጨምሮ በ10 ግለሰቦች ላይ ነው ወሳኔውን ያሳለፈው፡፡
ተከሳሾቹ እንደ አውሮፓያኑ አቆጣጠር በ2011 በግብፅ በተቀሰቀሰው አብዮት 20 ሺህ የሚሆኑ እስርኞችን እንዲያመልጡ በማገዝና ከውጭ ታጣቂ ሃይሎች ጋር በማሴር የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት ለአደጋ በማጋለጥ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸውን ገልጿል፡፡
ፍርድ ቤቱ ባለፈው ወር እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2013 በግብፅ በተቀሰቀሰ ህዝባዊ አመፅ የተሳተፉ የሙስሊም ወንድማማቾች አመራሮችን ጨምሮ በ12 ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት መወሰኑም ተሰምቷል፡፡
በመካለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ የአመነስቲ ኢንተርናሽናል የምርምርና አድቮኬሲ ይሬክተር የሆኑት ፊሊፕ ሉተር በግብፅ የሚከናወነው የሞት ፍርድ የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት አዛብቶታል ብለዋል፡፡
ሉተር አክለውም ግብፅ ተከሳሾችን በሞት በመቅጣት ከዓለማችን ሀገራት ሶስተኛዋ ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ በሀገሪቱ ከፍተኛ ይግባኝ ፍርድ ቤት የተላለፈው የቅጣት ውሳኔም የመጨረሻውና ሌላ ይግባኝ የማያስጠይቅ ነው ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button