Ethiopia

የሕወሃት ትንኮሳ በሰብዓዊ ድጋፍ ስርጭት ላይ የፈጠረው ጫና…

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013 አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን ወደሌሎች ክልሎች በማስፋቱ የእርዳታ እህል ለማጓጓዝ መቸገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ:: መንግስት ለሰብአዊ ድጋፍ ሲል ያሳለፈውን የተናጠል ተኩሱ አቁም አሸባሪው ህወሓት ወደ ጎን በመተው ትንኮሳውን ወደ አማራ እና አፋር ክልል ማስፋቱ ይታወቃል።
በዚህ ግጭት ምክንያትም የእርዳታ እህል እና መሰል ድጋፎችን ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት መቸገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ፋርሃን ሀቅ እንደገለጹት፤ በመንግስትና በዚህ አማጺ መካከል ባለው ግጭት ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ በተሽከርካሪዎች ሲጓጓዝ የነበረውን የእርዳታ እህል ወደ ትግራይ ክልል ማስገባት አልተቻለም።

ቃል አቀባዩ አያይዘው እንደተናገሩት፤ የእርዳታ ሰራተኞችን፣ ምግብ፣ ነዳጅ እና ሌሎች ሰብአዊ አቅርቦቶችን የጫኑ ከባድ መኪናዎች ከሰመራ ከተማ ወደ ትግራይ በሚወስደው መንገድ ላይ ተዘግቶባቸው መንቀሳቀስ አልቻሉም። በቀጣይ ቀናት የረድኤት ሰራተኞችን እና እንደ ነዳጅ ያሉ አቅርቦቶችን ወደ ትግራይ ማስገባት ካልተቻለ አንድ አንድ ሰብአዊ ድጋፎች እንደሚቋረጡም ያለውን ስጋት ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል። ድጋፉን በአውሮፕላን ለማድረግ በመንግስት በኩል እድሉ እንደተመቻቸላቸውና እቅድ መያዙንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ክልል የእርዳታ እህል ጭነው የሚጓጓዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሽብር ጥቃት በመፈጸም የእርዳታ መስመር እንዲዘጋ ማድረጉን የብሄራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ገልፆ ነበር፡፡ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መቐለ 2ኛውን በረራ እንደሚያደርግ መንግስት መግለጹም ይታወቃል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button