World News

ሳዑዲ አረቢያ የኮቪድ -19 ክትባት ለወሰዱና ከተለያዩ ሀገራት ለመንፈሳዊ ጉዞ ወደ መካ መዲና የሚገቡ የኡምራ ተጓዦች መቀበል እንደምትጀመር አስታውቃለች ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 ሳዑዲ አረቢያ የኮቪድ -19 ክትባት ለወሰዱና ከተለያዩ ሀገራት ለመንፈሳዊ ጉዞ ወደ መካ መዲና የሚገቡ የኡምራ ተጓዦች መቀበል እንደምትጀመር አስታውቃለች ፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ ከሰኞ ጀምሮ የኡምራ ተጓዦችን ጥያቄ መቀበል መጀመራቸውን ነው የገለጹት ፡፡ ሳዑዲ አረቢያ በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ለ18 ወራት ከተለያዩ ሀገራት መግቢያ በሮቿን ዝግ አድርጋ ቆይታለች፡፡ አሁን ላይ ከየትኛውም ሀገር የሚመጣ ተጓዥ የኮቪድ-19 ክትባት ስለመከተቡ የሚገልፅ ማስረጃ ካቀረበ ከነሃሴ አንድ ጀምሮ ወደ መካ መዲና መግባት እንደሚችል ፍቃድ አስተላልፋለች፡፡

እንደ አልጀዚራ ዘገባ ከሆነ ባለፈው ወር ወደ 60 ሺህ የሚጠጉ የኮቪድ -19 ክትባት የወሰዱ ዜጎች በሃጂ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ላይ እንዲሳተፉ መደረጉን ገልጿል፡፡ መካን በየወሩ 60 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከተለያዩ ሀገራት የሚጎበኙት ሲሆን ቁጥሩን በማሳደግ በወር እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች እንዲጎበኙት ለማደረግ ሳዑዲ ዕቅድ አስቀምጣለች፡፡ አሁን ላይ ሳዑዲ አረቢያ 532 ሺህ የሚጠጉ ዜጎቿ በኮቪድ የተያዙባት ሲሆን 8 ሺ 300 የሚሆኑት ደግሞ ለህልፈት ተዳርገውበታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button