COVID-19Ethiopia

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ10 ሺህ 804 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሺህ 95 ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል።13 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን፤ 532 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 282 ዜጎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button