Featured

በመስቀል በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ርችት መተኮስ የተከለከለ መሁኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 በመስቀል በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ርችት መተኮስ የተከለከለ መሁኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ከዚህ ቀደም ፖሊስ ያስተላለፈውን መልዕክት በመተላለፍ ርችት የተኮሱ ግለሰቦች ተይዘው በፍርድ ቤት እስከመጠየቅ መድረሳቸውን ነው ነፖሊስ የገለጸው፡፡
በበዓላት ወቅት የሚተኮሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ ሰላምን የማደፍረስ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች በሕገ-ወጥ መንገድ የገዙትን የጦር መሣሪያ እንደሚፈትሹ እና የተለያዩ የፀጥታ ስጋቶችን እንደሚፈጥሩ ፖሊስ አስታውሷል፡፡

የሕገ-ወጦቹን ድርጊት ለመከላከል እንዲቻል መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ አይችልም ነው የተባለው፡፡ ጳጉሜ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ለመስከረም 1 አጥቢያ ከለሊቱ 11 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ሦስት ግለሰቦች ርችት ሲተኩሱ ተይዘው ምርመራ ተጣርቶባቸው እያንዳንዳቸው በ4 ሺህ ብር ዋስ ተለቀው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑም ተገልጿል፡፡በተመሳሳይ በቦሌ፣ በቂርቆስ እና በየካ ክፍለ ከተሞች ርችት ሲተኩሱ የተገኙ ግለሰቦች ጉዳይም በምርመራ ሂደት ላይ እንደሚኝ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button