AfricaFeaturedPoliticsSocial

የዓለም አቀፍ ምሁራን ግልፅ ደብዳቤ ለአንቶኒዮ ጉቴሬዝ

በመላው ዓለም ከፍተኛ ተደማጭነትና ተፅዕኖ ያላቸውና አሜሪካና ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ አህጉራት የሚገኙ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ምሁራን እና የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች፣ በትግራይ ክልል በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካላት ሲፈፀሙ የታዘቧቸውን ሚዛናዊነት የሌላቸው ተግባራት በግልፅ በመናገራቸው፤ በድርጅቱ የሥራ ዕገዳ የተጣለባቸው ሁለት የመንግሥታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪዎች አስፈላጊ ከለላ እንዲደረግላቸውና ወደሥራቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ ግልፅ ዓለም አቀፋዊ ደብዳቤ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከሰዓታት በፊት ማስገባታቸውን አርትስ ቴሌቪዥን በተለይ በደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

እነዚሁ ሁለት ሴት የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪዎች ያዩትንና የታዘቡትን የአሠራር ሚዛናዊነት ማጣት፣ አድልዎ እና ሆን ብሎ መረጃዎችን የማዛባት እንቅስቃሴ በግልፅ ለጋዜጠኛ በመናገራቸው፣ “ያልተፈቀደ ቃለ መጠይቅ በመስጠት” በሚል በድርጅቱ የበላይ ኃላፊዎች ትዕዛዝ ከሥራቸው ላይ መነሳታቸው በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል።

በዚሁ አግባብ ያልሆነ ጉዳይ ላይ ምሁራኑ እና የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች በፃፉት እና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ በአድራሻ መጻፉን አርትስ ቲቪ ማረጋገጥ የቻለው ደብዳቤ “በሁለት ጥቁር ምስጢሩን በይፋ የተናገሩ ጥቁር ሴት ሠራተኞች ላይ የተወሰደውን አግላይና ኢፍትሃዊ ርምጃ በሚመለከት” በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሌሎች ግልፅ የሆነ አድልዎ የሚፈፅሙና ከድርጅቱ መርህ ጋር በቀጥታ የሚቃረኑ ተግባራትን በትግራይ የሚፈፅሙ የድርጅቱ ሠራተኞችን እንዳላየ በማለፍ እነዚህን ሁለት ሴት ሠራተኞች ዕውነቱን ስለተናገሩ ብቻ ከሥራ ማገድ አግባብነት የሌለው ግልብ ርምጃ መሆኑን በጠንካራ ቋንቋ ግልፅ ማስረጃዎችን በመጥቀስ በዝርዝር መረጃዎች የተሟላ ሲሆን፤ ድርጅቱ ዕውነትን ለመናገር በደፈሩ የኢትዮጵያ ተጠሪዎቹ ላይ በወሰደው በዚህ አግባብነት በሌለው ውሳኔ ምክኒያት በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ቁጣ የፈጠረ ሲሆን፤ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የቆሙ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሠሩ የተለያየ ሃገር ዜጐችና የተለያዩ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች የሚያስተምሩ ምሁራንም የተቃውሞ ድምፃቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እያሰሙ ይገኛሉ። ይህንኑ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ የሚያስተባብሩት በካናዳው ባሲል ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት አን ፊትዝ ጄራልድ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።

ከሠዓታት በፊት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እንዲደርስ የተደረገው ከላይ የተጠቀሰው ደብዳቤም የዚህ አካል ሲሆን፣ አርትስ ቲቪ የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ማግኘት የቻለ በመሆኑ፣ ተመልካቾቻችን የደብዳቤውን ይዘት በአርትስ ቲቪ ዌብ ሳይት፣ የትዊተር፣ የፌስ ቡክ፣ ኢንስታግራም ገፆች ላይ ማንበብ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።

ሙሉ ደብዳቤው፡ http://www.artstv.tv/wp-content/uploads/2021/10/Open-Letter_-to_UN_Secretary_General_2021-Oct-15.pdf

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button