Ethiopia

የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 28፣ 2013 የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ፡፡ የተፈናቀሉ ዜጎች በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ”ይጠይቁ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የማህበራዊ ሚዲያ የተሳትፎ መድረክ ለቀረቡ ጥያቄዎች በቦርዱ የፌስቡክ ገጽ በቀጥታ ምላሽ ሰጥተዋል።

የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው በምን አይነት መልኩ ይሳተፋሉ? በሚል ከተሳታፊ ለተነሳው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው ላይ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ቦርዱ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል። ዜጎቹ ባሉበት ቦታ ሆነው የሚመዘገቡበትና ከመጡበት አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች
ምርጫውን የሚያደርጉበት ሁኔታ መመቻቸቱን አመልክተዋል።

ምርጫ ቦርድ የተፈናቀሉት ዜጎች የሰጡትን ድምጽ ከመጡበት አካባቢ ሰዎች ከሚሰጡት ድምጽ ጋር የሚደመርበት የውጤት ማስላት ዘዴ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል። በአዲስ መልክ ዜጎች የተፈናቀሉባቸው ቦታዎች በመኖራቸው የወቅቱን መረጃዎች ማወቅ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል። ለዚህ ደግሞ የሰላም ሚኒስቴርና የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) የሚያወጧቸውን መረጃዎች መሰረት በማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የተፈናቀሉ ዜጎች ባሉባቸው አካባቢዎች ለመራጮች ትምህርት ለመስጠት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላና ሌሎች በተጓዳኝ የሚከናወኑ ስራዎች የሚመሩበት እቅድ
መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button