Africa

ለ12 ሰዓታት ዋኝተው ህይዎታቸውን ከአደጋ ያዳኑት የፖሊስ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 ሄሊኮፕተራቸው ባህር ላይ የወደቀችባቸው የማዳጋስካር የፖሊስ ሚኒትስር ለ12 ሰዓታት ያህል ዋኝተው
ራሳቸውን ማዳናቸው ተሰማ፡፡ ሚኒስትሩ ሰርጌ ጌሌ ከሄሊኮፕር አደጋው በህይወት ከተረፉት ሁለት ሰዎች መካከል እንዱ ናቸው
ተብሏል፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው የ57 ዓመቱ ጌሌ ለ12 ሰዓታት ያህል ከዋኙ በኋላ ማሃምቦ በተባለች የባህር
ዳርቻ አቅራቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችና ዓሣ አጥማጆች አግኝተዋቸው ወደ ህክምና ወስደዋቸው ነው
በህይወት የተረፉት፡፡


ሚኒስትሩ የህክምና እርዳታ ካገኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት አሁን ከሞት አፍ አምልጫለሁ፤ ለዚህም
ፈጠሪን፣ የመንደሪቱን ነዋሪዎችና ዓሣ አጥማጆችን ከልቤ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
የማዳስካር ፖሊስ ሃላፊ በመግለጫቸው ጌሌ ሁሌም ስፖርት የሚያዘወትሩና ጠንካራ ሰው ባይሆኑ ኖሮ
አሁን ላይ በህይዎት አናገኛቸውም ነበር በማለት ራሳቸውን ለማዳን ያደረጉትን ብርቱ ጥረት አድንቀዋል፡፡


ሚኒስትሩና ባልደረቦቻቸው 130 ሰዎችን ጭና ስትጓዝ አንሴራካ በተባለ ስፍራ የሰመጠች መርከብን
ሁኔታ ለማየት ሲጓዙ ነበር የሄሊኮፕተር አደጋው የደረሰባቸው፡፡
የሄሊኮፕሯ አብራሪና አንድ የፖሊስ ባልደረባ እስካሁን የገቡበት ያልታወቀ ሲሆን ህይወታቸው ሳያልፍ
እንደማይቀር ጥርጣሬ አለ ነው የተባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button