Ethiopia

2 ሺህ 921 የጤና ተቋማት ወድመዋል-የጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 በአሸባሪውቹ ህወሃት እና ሸኔ በአራት ክልሎች 2 ሺህ 921 የጤና ተቋማት መውደማቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጎማ ለፋና እንደተናገሩት በአማራ፣ አፋር ፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እና ኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች በሽብር ቡድኖቹ የጥፋት እጆች የጤናው ሴክተር ቀዳሚ ውድመት ደርሶበታል ብለዋል።


በአማራ ክልል 40 ሆስፒታሎች፣ 450 ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች በፀረ ህዝብ ቡድኖቹ በመውደሙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። የጤና አገልግሎትን የፀጥታ መደፍረስ ባለባቸው የድንገተኛ አገልግሎት በማሰማራት፣ በጦርነቱ ተንቀሳቃሽ ህክምና በመስጠት እና በወደሙ አካባቢዎች መልሶ በመገንባት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ
ጥረት ተደረጓል ነው ያሉት ዶክተር ደረጀ ዱጎማ። በዚህም 600 ሚሊዮን ብር የህክምና ቁሳቁስ እና መድሃኒቶች ውድመት ወደ ደረሰባቸው አካባቢዎች
ሚኒስቴሩ ማንቀሳቀሱን ተናግረዋል።


ይህም የደሴ፣ ሀይቅ እና ኮምቦልቻ ጨምሮ 11 ሆስፒታሎችን በፍጥነት በማቋቋም ተፈናቅለው ለነበሩ ወገኖች ህክምና መስጠት ተችሏል። በአዲስ አበባ ያሉ የመንግስት ሆስፒታሎች፣ የግል ሆስፒታሎች እና ዲያስፖራዎች መልሶ በማቋቋሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ነው ያሉት። በጦርነቱ ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ህፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ህክምና እንዳያገኙ በማድረግ የሰነ ልቦና እገዛ እንዲያገኙም መደረጉን ነው ሚኒስትር ዴኤታው ያነሱት። ከችግሩ ግዝፈት አንጻር ግን ሁሉም ቦታዎች ላይ ተደረሷል ማለት አይደለም ሲሉም ገልፀዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button