Politics

በጦርነት የወደሙ ከተሞችን መልሶ ለማቋቋም 58 ከተሞች የጥምረት ስምምነት መፈራረማቸውን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 በጸጥታ ችግር ጉዳት የደረሰባቸውን ከተሞች መልሶ የመገባንት ሂደት በተፋጠነ መልኩ ለማስኬድ የሚያግዝ አሰራር መዘርጋቱንም አስታውቋል። ሚኒስቴሩ የበጀት ዓመቱት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን፤ በቤቶች ግንባታ፣ በመሬት አቅርቦትና የግንባታውን ዘርፍ በማዘመን፣ ከተሞችን ለነዋሪዎች የተሻለና ምቹ በማድረግ የአሰራር ማዕቀፍ መዘርጋቱ ተገልጿል።


የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፋንታ ደጄን እንዳሉት፤ አሸባሪው ህወሓት ወረራ ፈጽሞ በነበረበት ወቅት በከተሞችና መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አድርሷል። በአማራና አፋር ክልሎች ለከፍተኛ ጉዳት የተዳረጉ ከተሞች ነዋሪዎች የዕለት ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻል ሚኒስቴሩ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል። በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ከተሞች በአፋጣኝ መልሶ ለመገንባትና ከነበረው የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ከተሞች የሚረዳዱበት የትስስር ስርዓት መመቻቸቱን አስታውቀዋል።


በዚህም 58 ከተሞች የጥምረት ስምምነት መፈራረማቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ከተሞቹ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያደርግ ስራ እንሰራለን ብለን ነው ያቀድነው ብለዋል። አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የክልል ከተሞች የቤት ፍላጎትና እጥረት ችግር ማቃለል እንዲቻል የግል አልሚዎች የሚሳተፉበት አሰራር መዘርጋቱንም ጠቅሰዋል። እንደሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፤ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በማህበር እየተደራጁ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የሚያገኙበት አሰራር በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል ጥረት እየተደረገ ነው።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button