Africa

በሴኔጋል በአንድ ሆስፒታል በተከሰተ የእሳት አደጋ የ11 ህፃናት ህይወት ማለፉ በሀገሪቱ ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሯል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 በሴኔጋል በአንድ ሆስፒታል በተከሰተ የእሳት አደጋ የ11 ህፃናት ህይወት ማለፉ በሀገሪቱ ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሯል ተባለ፡፡
የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በጨቅላ ህፃናቱ ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ በሰማሁ ጊዜ ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት መልእክትም ለህፃናቱ ወላጆችና ለመላው ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ በማለት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡


የጤና ሚኒስትሩ አብዱላየ ዲዩፍ ሳር በበኩላቸው ሁኔታው በእጅጉ የሚያሳዝንና ልብ የሚነካ ነው ብለዋል፡፡ የችግሩ መንስኤ እየተጣራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ጄኔቫ ላይ እንዳሉ ነው ሀዘናቸውን የገለፁት፡፡ በሆስፒታሉ የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎ በፍጥነት በመሰራጨቱ ሳቢያ ከሶስት ህፃናት በላይ ማዳን
እንዳልታቸለ የከተማዋ ከንቲባ መናገራቸውን አፍሪካ ኒውስ ነው የዘገበው፡፡


አደጋው በሴኔጋል ያለው የህዝብ ጤና አጠባበቅ ሲስተም ደካማ ስለመሆን አንዱ መገለጫ ነው በማለት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ ለዚህ ማሳያ ደግሞ ባለፈው ሚያዚያ ወር አንዲት የ9 ወር ነፍሰጡር ከ20 ሰዓታት በላይ በህመም ስትሰቃይ በቂ የህክምና ድጋፍ ባለማግኘቷ ምክንያት መሞቷንና ጉዳዩ በፍርድ ቤት መያዙን በዋቢነት ጠቅሰዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button