Uncategorized

የቴክኖው CAMON 17 ሰልፊ ላይ ባውጠነጠነ አስገራሚ ዘጋቢ ፊልም በመታገዝ ወደገበያ ገብቱዋል::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 የቴክኖው CAMON 17 ሰልፊ ላይ ባውጠነጠነ አስገራሚ ዘጋቢ ፊልም በመታገዝ ወደገበያ ገብቱዋል::ይህ ፈጠራ የታከለበት በፊልም የታገዘው የቴክኖ የማስመረቂያ ፕሮግራም ድርጅቱ ምርቱን ከማስተዋወቅ ባለፈ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና በሰብዓዊነት ላይ የበለጠ ጥረት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው:: ይህ ደግሞ ድርጅቱ በአለማችን ላይ በዘርፉ ቁንጮ እየሆነ መምጣቱን ይጠቁማል::

በአዲሱ ትውልድ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ቴክኖ ሞባይል በ ግንቦት 4 2013 ላይ በለቀቀው አዲሱ የCAMON 17 ተከታታይ ስልክ የብዙሆችን ቀልብ መሳብ ችሉዋል:: በማስመረቂያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ሰዎች ወደ ትዕይንቱ ሲገቡ፣ በሰልፊ እና በሰልፊው ትውልድ ፍላጎት ዙሪያ ትኩረት ባደረጉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያብራራ አስደናቂ ዘጋቢ ፊልም ላይ እዲታደሙ ተደርገው ነበር። ዝግጅቱ እየገፋ ሲሄድ ተሰብሳቢዎቹ በእርግጥ
TECNO የዚህን ወጣት ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት በተጨባጭ እና በስሜት እየሰራ መሆኑን ተገንዝበዋል::

“The rise of selfie” በሚል ርዕስ የቀረበው ዘጋቢ ፊልም ስለሰልፊ አመጣጥ እና እንዴት ሰልፊ የአሁኑ ትውልድ መገለጫ መሆን አንደቻለ ያወራል:: የቴክኖ አዲስ የንግድ አምባሳደር የሆኑት የሆሊውድ ተዋናይ ክሪስ ኢቫንስ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል፣ሕያው እና በስሜት የተሞላ ምስል ትፈልጉ ይሆናል ወይም ቀላል የሆነ ነገር ትፈልጉ ይሆናል"፣ ነገር ግን መልካም ምስል የሚያደርገው እጅግ ግለሰባዊ" ስለሆነ ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም ቴክኖ በፅኑ ከሚያምንበት እና ከሚታወቅበት ሃሳብ ጋር ይጣጣማል:: የስማርት ስልክ ፅንሰ ሃሳብ ብራንዱ ላይ ሳይሆን ተጠቃሚው ላይ ማውጠንጠን አለበት::

TECNO CAMON 17 ሁልጊዜ በልባቸው ወጣት ለሆኑ እና ለአዳዲስ ነገሮች ራሳቸውን ለሚያነሳሱ ተጠቃሚዎች ምልክት
ለመሆን የተሰራ ሲሆን ፣ ሰዎች እራሳቸውን በይበልጥ ለመግለጽ እንዲችሉ ያስችላቸዋል::

ዶክመንተሪው መጪዊን ግዜ የምንመለከትበትን መንገድ ያሳያል ። ከዲጅታል ትውልዱ እንደተረዳነው ለግለሰቦችም ሆነ ለቡድኖች
ኦንላይንም ሆነ ኦፍ ላይን ሰልፊ እራስን ለመግለፅ አማራጭ መንገድ ነው::
ፊልሙ የስነ-ልቦና ፕሮፌሰር ባለሙያውን ቶማስ ከርራን እና ፎቶግራፍ አንባቢውን ዩጄኒ ሺንከልን፣ እንዲሁም ቴክ ጋዜጠኛ ሉሲ
ሄጅስ፣ በፎቶግራፍ ላይ ያላቸውን ጠቃሚ ግንዛቤ አካፍለዋል። በመድረኩ ላይ ለታዳሚው ስለ ሰልፊ ብዙም ያልተነገረላቸው

ሃሳቦችን በማካፈል ታዳሚው ስለሰልፊ የተሻለ ግንዛቤ አንዲኖረው ኣድርገዋል:: ይህም ታዳሚውን ስለዚህ ትውልድ ልማድ እና
እዴት TECNO CAMON 17 ለተጠቃሚዎቹ በጣም ተስማሚ የሆነበትን ምክንያት ለመረዳት አስችሎታል::

የፋሽን ሞዴል የሆኑት ሣራ ዮሐንሰን በፊልሙ ላይ፣ ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎች ዕራሳቸው ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የሚያስችላቸውን
መንገድ በምሳሌ አስፍረዋል። በፊልሙ ላይ CAMON 17 ይዘው በመታየት የስልኩን የሚያምሩ ዝርዝር ገፅታዎች እና የሰልፊ
ክህሎቶችን አንፀባርቀዋል::
የፋሽን ሞዴል የሆኑት ሣራ በፊልሙ ላይ እንዳሉት፣ እንደ TECNO CAMON 17 ያሉ የሰልፊ ስልኮች ተጠቃሚዎች የራሳቸውን
ምስል ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ምርጥ የሆኑ ፎቶዎችን በማንሳት ምስላቸውን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል::
በተጨማሪም የተሻለ ማንነት እንዲኖረን ለማድረግ እዲሁም በደመ ነብስ ወደተሻለ እኛነት እንድንመጣ ለራሳችን የምንጠቁምበት
መንገድ ነው:: ይህም ደግሞ የሰልፊ ዋነኛ ጥቅም ነው::
የTECNO CAMON 17 በጣም የተሻሻሉ መገልገያዎችን የያዘ ሲሆን next generation የሆነውን TAIVOS 2.0
በመጠቀም የካሜራ setting በማሻሻል ከአካባቢያችን ካለው ነገር ጋር የተጣጣመ ምስል እንድናገኝ ያስችላል:: ይህ ሁሉ
በግልጽ በተቀመጠ የፊት ካሜራ ይያዛል::

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሰልፊ ማኅበራዊ ክስተት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ከመሆኑም በላይ ሰዎች ሐሳባቸውን የሚገልጹበት
ዋነኛ መንገድ ሆኗል:: ኮቪድ-19 ባስከተለው ተጽዕኖ ምክንያት ዓለም ለዘለቄታው ተለውጧል፤ ሰዎች ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር
በሰላም ለመገናኘት ሰልፊን በማዘውተራቸው የሰልፊ ተግባር ይበልጥ አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል። ይህን የደንበኞች ሰልፊ አጠቃቀም
ቴክኖ እና ሌሎች የስልክ አምራቾች በአጽንኦት እንዲያጤኑት አድጉዋቸዋል::

የቴክኖው CAMON 17 የስማርት ስልክ ገበያ ላይየዋለበት ግዜ ለደንመኞች ፍፁም አመቺ ጊዜ ላይ ነው:: ተጠቃሚዎች ከራስጌዎቻቸው ተጨማሪ ነገር የሚፈልጉ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ጥራት ያለው ካሜራ ያለው ስማርትፎን ያደንቃሉ፤ እንዲሁም የፈጠራ ችሎታቸውን የመመርመር ነፃነት ይሰጣቸዋል። የቴክኖው CAMON ተከታታይ ስልክ ለቴክኖሎጂ ቅርብ ላልሆኑ ሰዎች እንኩዋን ፎቶ የማንሳት ሂደቱን በጣም አስደሳች አድርጎታል:: በCAMON17 ስልክ ሰዎች ህይወት ያላቸው የሚመስሉ ፎቶዎችን ማጣጣም ብቻ ሳይሆን በ FHD ስክሪን ላይ በጣም ግልጽ የሆነ ምስልን ማየትይችላሉ:: ይህ ከፍተኛ ጥራት ያለው ስክሪን ተጠቃሚዎች በቪዲዮ ጥሪዎች ላይ በሚሆንበት ግዜ ተወዳዳሪ የሌለው ግልጽነት ይሰጣቸዋል:: በተጨማሪም ከፍተኛ ጥራትያላቸው ቪዲዮዎችን መመልከት እና ኃይለኛ አቅም የሚፈልጉ ጌሞችን መጨዋት ይችላሉ።

በዚህ የምርት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም ላይ የሰልፊን ታሪክ የሚቃኘው አዲስ ክስተት ቴክኖ ምርቱን ከማስተዋወቅ ባለፈ በኢንዱስትሪ ፣ በማኅበራዊና በሰብዓዊ አስተሳሰብ ረገድም የበለጠ ጥረት ለማድረግ የሚያደርገውን ተነሳሽነት የሚያንጸባርቅ ነው። ቴክኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ ታዋቂ ዓለም አቀፍ የስልክ ኢንዱስትሪ መሪ እየሆነ እንደመምጣቱ በመሰል ፊልሞች የዓለም አቀፉን ህብረተሰብ ስለሰልፊ ያለውን አስተሳሰብ ለማሳደግ መስራቱ እይታውንና ጉልምስናውን እያሳየ ነው ።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button