Africa

ሱዳን የሽግግር መንግስትና በተቃዋሚ ሃይሎች የተጀመረው የሰላም ድርድር አሁንም እክል ገጥሞታል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 በ እስካሁን በተደረጉ ውይይቶች በፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባቶች ቢኖሩም በማእከላዊ መንግስትና በክልሎች መካከል በሚኖረው የሥልጣን ውክልና መስማማት አልተቻላቸውም፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የሱዳን ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄን ወክለው የሚደራደሩት አማር አሞን ዋና ዋና ሀገራዊ ስምምነቶች ወደፊት በህዝበ ውሳኔ እንዲረጋገጡ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

በተለይ በሁለቱ ሃይሎች መካከል አለመግባባት እንዲካረር ያደረገው ዋነኛ ምክንያት ከ60 ዓመታት በላይ ስልጣን በማእከላዊ መንግስት ተይዞ መቆየቱ ነው ብለዋል ተደራዳሪው፡፡ ሱዳንን የሚመራው የሽግግር መንግስት በሰሜናዊ ሱዳን ከፍተኛ ተቀባይነት ካለው የሱዳን ህዝቦች ንቅናቄ ጋር የጀመረው ድርድር ባለመስማማት በተደጋጋሚ ያለውጤት ሲበተን ቆይቷል፡፡

ሌላው ሁለቱን ወገኖች የማያስማማቸው ጉዳይ የጦር ሃይሉ አደረጃጀት ምን መምሰል አለበት ሚለው ጉዳይ ሲሆን አሁንም መቋጫ አላገኘም ነው የተባለው፡፡
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ ወዲህ የተቋቋመው የሱዳን የሽግግር መንግስት ነፍጥ አንግበው ከሚዋጉ ሃይሎች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተወያይቶ እርቅ ማውረድን ተቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ ቢንቀሳቀስም እስካሁን ይህ ነው የሚባል ውጤት ማምጣት አልተቻለውም ነው የተባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button