World News

በጠቅላይ ሚኒስትራቸው እምነት ያጡ የእንግሊዝ ሚኒስትሮች ስራ መልቀቅ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 በእንግሊዝ በጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እምነት አጣን በማለት የሥራ መልቀቂያ የሚያስገቡ ባልስልጣናት ተበራክተዋል ተባለ፡፡ በርካታ ሚኒስትሮች ከጆንሰን ጋር መስራት እደማይችሉ በመግለፅ ነው የሥራ መልቀቂያቸውን ያስገቡት ተብሏል፡፡


የአብዛኞቹ ምክንያት ተመሳሳይ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩና አስተዳደራቸው ላይ ያላቸው እምነት ከእለት ወደ እለት እየተሸረሸረ መምጣቱ መሆኑን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡ በትናንትናው እለት የሥራ መልቀቂያ ያስገቡት የህጻናትና ቤተሰብ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዊል ኩይንስ ለሚዲያዎች ማብራሪያ እንድሰጥበት የተሰጠኝ መረጃ የሀሰት መሆኑን ካወኩ በኋላ በስራዬ ላይ መቆየት እንደማልችል አረጋግጫለሁ ብለዋል፡፡


ይህን የሀሰት መረጃ የሠጡኝ የጆንሰን የቅርብ ሰዎች ናቸው ያሉት ኩይንስ ስራን በድንገት መተው ቀላል ውሳኔ ባይሆንም እኔ ግን ይህን ማድረጌ ትክክል ነው በማለት ገልጸዋል፡፡ የጤናና የፋይናንስ ሚኒስትሮቹም ስራችውን መልቀቃቸውን ያሳወቁ ሲሆን ምክንያታቸውን በደፈናው የቦሪስ ጆንሰን አስተዳደር ከስህተቱ የማይማር መሆኑን ተገንዝበናል የሚል ነው፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ዘርፍ ረዳት የሆኑት ላውራ ትሮት በበኩላቸው ስራቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ካሳወቁ በኋላ በጆንሰን አስተዳደር መተማመን ጠፍቷል ብለዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ጆንሰን ከባድ ፈተና ውስጥ የገቡ ሲሆን መንበራቸው የመነቃነቅ አደጋ የገጠመው
መሆኑን የፖለቲካ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button