Ethiopia

አሸባሪዉ ህዉሃት ሰቆጣን ለመቆጣጠር ያደረገዉ ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳይሳካ የሰቆጣ ወጣቶች ተደራጅተዉ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነዉ ሲል ተደራጅተዉ አከባቢያቸዉን ከሚጠብቁ ወጣቶች አንዱ የሆነዉ ሙሉቀን ዳኘዉ ለአርትስ በስልክ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 አሸባሪዉ ህዉሃት ሰቆጣን ለመቆጣጠር ያደረገዉ ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳይሳካ የሰቆጣ ወጣቶች ተደራጅተዉ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነዉ ሲል ተደራጅተዉ አከባቢያቸዉን ከሚጠብቁ ወጣቶች አንዱ የሆነዉ ሙሉቀን ዳኘዉ ለአርትስ በስልክ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ በተለይም የተደራጀዉ የአካባቢዉ ወጣት ሃይል ህዝቡ ከተማውን ለማንም ጥሎ እንዳይወጣ የማረጋጋትና ማንኛውም የታጠቀ ሃይል በአንድ ኮማንድ ስር ሆኖ በፈረቃ ከተማውን እንዲጠብቅ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የከተማዉ ነዋሪ ሙሉቀን ዳኘዉ ገልፅዋል፡፡

ይሁን እንጂ በሰቆጣ የተለያዩ መንገዶች በመዘጋታቸዉ ምክኒያት ምግብ ነክ እና አጠቃላይ ሸቀጦች ወደ ከተማዉ መግባት ያልቻሉ በመሆኑና ዉሃና መብራትም ባለመኖሩ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸዉን ወጣት ሙሉቀን ነግሮናል፡፡ በመሆኑም ህዝቡ ለከፋ ችግር ከመጋለጡ በፊት መንግስት የምግብ አቅርቦት እና የተለያዩ አቅርቦቶችን ድጋፍ እንዲያደርግ ወጣት ሙሉቀን አሳስቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button