World News

የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እውን መሆኑን ተከትሎ የቻይና ከፍተኛ እርምጃ እየተጠበቀ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እውን መሆኑን ተከትሎ የቻይና ከፍተኛ እርምጃ እየተጠበቀ ነው ተባለ፡፡ ያለፉት ጥቂት ቀናትን ቀልብ ስቦ የነበረው የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታየይዋን ጉብኝት ማክሰኞ ምሽት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የቻይና የአስፈሪ እርምጃ ማስጠንቀቂያዎች በተከታታይ እንደሚሰሙ መገናኛ ብዙሃኑ እየዘገቡ ይገኛል፡፡፡ ቤጂንግ በአፈ-ጉባኤዋ ጉብኝት ብስጭቷን የገለፀች ሲሆን እንደ ራሷ ግዛት የምትቆጥራት ታይዋንን
በዚህ ደረጃ እውቅና መስጠት የቻይናን ሉአላዊነት እንደመጣስ ይቆጠራል ሲል የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡


ፔሎሲን የያዘው አውሮፕላን የታይፔን ምድር በረገጠ ቅፅበት ቻይና በታይዋን የውሃ ክልሎች የረዥም ርቀት ጥቃቶችን ያጠቃለለ ለቀናት የሚቆይ ወታደራዊ ልምምዶችን እንደምታደርግ አስታውቃለች ፡፡ ቤጂንግ እነዚያ ልምምዶች ሐሙስ እንደሚጀምሩ የገለፀች ሲሆን በእነዚያ ጊዜያት የውጭ ሀገራት መርከቦች እና አውሮፕላኖች ወደ ቀጠናው እንዳይገቡ ጠይቃለች ።

በታይዋን ዙሪያ ያሉ ባሕሮች በማጓጓዣ አገልግሎት የተጠመዱ ሲሆን ታይዋን ቻይና የወሰደችው እርምጃ የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ እገዳ ነው ብላለች። ቻይና በታይዋን እና በግዛቷ መካከል ያሉ በርካታ የምርት ንግድ የታገዱ ሲሆን ከ100 በላይ የታይዋን የምግብ ንግዶች የማእቀብ ሰለባ ሆነዋል። ከነጻነት ንቅናቄው ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸው ሁለት የታይዋን ድርጅቶችንም በጥቁር መዝገብ ውስጥ ከመካተታቸው በተጨማሪ በቻይና የሚገኙትን የአሜሪካ አምባሳደር ጠርታለች ሲል ቢቢሲ
አስነብቧል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button